የኢትዮጵያዊያን ማሕበረሰብ በኦተዋ 124ኛ የዓድዋን ድል በዓል መታሰቢያ ቅዳሜ ማርች 7 ቀን 2020 በብሮንሰን ማዕከል በደመቀ አክብሯል፡፡
የኢትዮጵያዊያን ማሕበረሰብ በኦተዋ 124ኛ የዓድዋን ድል በዓል መታሰቢያ ቅዳሜ ማርች 7 ቀን 2020 በብሮንሰን ማዕከል በደመቀ አክብሯል፡፡
በዕለቱም የምሕበሩ ሊቀመንበር አቶ ከፍያለው ገመዳ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ዝግጅቱን የከፈቱ ሲሆን፤ በንግግራቸውም የአድዋ በዓል የመላው የኢትዮጵያዊን በዓል መሆኑን በማውሳት እንግዶቻቸውን ያለምንም የፖለቲካ ሆነ የእምነት ልዩነት ይህንን የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን ሀገራዊ በዓል በደመቀ ሁኔታ በጋራ ለማሰብ መሰባሰባቸውን አመስግነው በኦታዋ የሚገኙ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብም ይህንንም መነሳሳት በማህበሩ እንቅስቃሴ ላይ በንቃት በመሳተፍ እንዲደግፉና የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም የእለቱ የክብር እንግዳ በካናዳ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በምክትል አንባሳደር ማዕረግ አምባሳደር ለገሰ ገረመው አባቶቻችን በህብረት ያገኙትን ድል የአሁኑም ትውልድ የራሱን ታሪክ በመስራት እንዲደግም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ በተለይ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ይህ ትውልድ የራሱን አሻራ የማስቀመጥ እድል እንዳለው እና አንደ ቀደመው ትውልድ በአንድነት የተጀመረውን ግድብ እንዲያጠናቅቅ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ለእለቱ ተጨማሪ ድምቀት የሰጡ በርከት ያሉ ዝግጅቶች የተካሄዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በወጣቶች እና ህጻናቶች የቀረቡ አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ፕሮግራሞች እንዲሁም በታዋቂ የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጁ ግጥሞች እና መነባንቦች ታዳሚውን እስከ ዝግጅቱ ፍጻሜ በጥሩ መንፈስ አንዲቆይ እስችለውታል፡፡
በመጨረሻም ለዚህ ዝግጅት መሳካት እስተዋጽኦ ላደረጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ማሕበሩ ያዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡